
ዳስተር /Eraser ከተቀመጠበት ለማንሳት ረጋ ብላችሁ እየተረዳመዳችሁ Hello my classmates ፡
Hello dear our ......(Subject) teacher;
ዳስተሩን አንስታችሁ ቦርድ እያጠፋችሁ ንግግራችሁን ሳታቋርጡ ቀጥሉ
Here we are going to see about ..........(your lesson topic)
e.g Here we are going to see about Modal verbs .....ቦርድ ላይ ቀን ካልተፃፈ ፃፉ ...about ስትሉ ቦርድ ላይ ከድምፃችሁ እኩል ፅፋችሁ ጨርሱ
ወደ ተማሪዎቹ ዞር ብላችሁ
So if you are ready ,let's began.ብላችሁ ሃተታችሁን መቀጠል....
So here we go.Philosophy means.... የሚል skeleton ተጠቅማችሁ ወደ ፕረዘንቴሽናችሁ መግባት
🔰ፕረዘንቴሽን ስናቀርብ ማድረግ ያለብን ነገሮች!
1️⃣ ሰዓት አጠቃቀም
❓የተሰጣችሁን ሰዓት በዓግባብ ካልተጠቀማችሁበት ማለት የምትፈልጉትን ሃሳብ ሳትናገሩ ወደመቀመጫችሁ ትሸኛላችሁ!ስለዚህ ጊዜ ለመቆጠብ ፦
1)አንድ ነገር እየደጋገማችሁ ለማስረዳት አትሞክሩ።
2) ለተማሪዎች ኖት ለመፃፍ አትሂዱ!ኖት ከመፃፍ ይልቅ ትናንት ባሳየኋችሁ ምሳሌ መሰረት draft ያደረጋችሁትን Outline በBullet & numbering ቦርዱን አሸብርቁት!
3) ጊዜ ለመቆጠብ ከፈለጋችሁ በምታወሯቸው ቃል ማህል እንደ ባለስልጣን ' እእእ...' እያላችሁ ንግግር አታቆርፍዱ! ሳዓት ያልቃል ፤ ንግግራችሁ ይደብራል ፤ ነጥባችሁንም ያስጎምዳል!
2️⃣ ቦታ አጠቃቀም
ሙሉ ቦታ ለመጠቀም ብላችሁ እንደ Dance choreography መድረኩን አትፈንጩበት!
ከመድረኩ ቀኝ ረድፍ ላይ መቆም ካለባችሁ ቆሙ ፤ በግራ መልኩ መሆን ካለባችሁ እንደዛው አክት አርጉ!ዘና በሉና
❗️Warning : calculation ከሆነ ቦርድ ላይ የምትሰሩት ተማሪዎችን ሳትከልሉ ፤ ራሳችሁን ከቦርዱ ወደ ዳር ገለል አርጋችሁ ማቀጣጠል ይኖርባችኋል!
ቦታ አጠቃቀም ላይ ጎበዝ ካልሆናችሁ የመድረኩ ማህከል ላይ ሁኑ!በግራም በቀኝም ፤ በማህልም ረድፍ ያሉ ተማሪዎች ትኩረታችሁን አይነፍጓችሁም!
3️⃣የሰውነት እንቅስቃሴ አጠቃቀም!
ጥናቶች እንደሚያሳዩት ''በቃል ለቃል ምልልስ'' ጊዜ የሰውነት እንቅስቃሴዎች ሃሳባችንን በ 30% ጭማሪ ቀላል እና ግልፅ ያረጉታል።ስለዚህ የሰውነት እንቅስቃሴያችሁ እንደሚከተለው ይሁን!
✅ የእጅ እንቅስቃሴ አጠቃቀም
1)እጃችሁን ከጭንቃላታችሁ በላይ አታወራጩ!...የሚመለከታችሁ ሰው ይደክመዋል
2) ነገሮችን በተለመዱ የእጅ መልክቶችን ለመግለፅ ሞክሩ!...ለምሳሌ
መሮጥ ከሆኑ ቃሉ እነ ሃይሌ ገ/ስላሴ ሲረጡ እጃቸውን እይደሚያረጉት ማሳየት ...
3) እጃችሁን ኪሳችሁ አታርጉ!...የጋጣወጥ ባህሪ አላችሁ ተብሎ ይታሰባልና
4) እያወራችሁ ሳለ እጃችሁን አትፈትጉ። የእጃችሁን ጣቶች ለማንቋቋት አትሞክሩ!እንደዛ ስታረጉ ሰው አይኑቹን እጃችሁ ላይ ያረጋል!ያኔ ድንብርብራችሁ ይወጣል!
5) አደራ እየፃፋችሁ የምትሳሳቱት ነገር ካያችሁ በእጃችሁ አታጥፉ!ምምህሩ እና ተማሪዎቹ ለናንተ ያላቸው ቦታ ይቀንሳል!ለምን አንድ ፊደል አትሆንም ከተሳሳታቹ በዳስተር አጥፉ!
✅ የእግር እንቅስቃሴ አጠቃቀም!
1).በተለይ ሴቶች 😡ጭነታችሁን በአንድ እግራችሁ ላይ አታርጉ!ቆፈጠን በሉ! የተመጣጠነ አረማመድ ይኑራችሁ!ላንዴ እንኳን ዘንበል የሚል አቋቋም እንዳይኖራችሁ!
✅ የጭንቅላት እንቅስቃሴ አጠቃቀም
1) ይሄ እንኳን ብዙ አይጠፋችሁም ፤ ራስ በመነቅነቅ የሚደረግ እንቅስቃሴ ነው!
4️⃣የአቀራረብ ዘዴ
1). ተማሪዉን የሚያሳትፍ ከባቢ ፍጠሩ!
ለተማሪዎች ስታስረዱ ጥያቄ ጠይቋቸው ፣ መልሳቸውንም እየሰማችሁ የተነቃቃ audience ያዙ!መምህሩ አሪፌ እንቅስቃሴ ሲያይ ደስ ይለዋል!
2).ፕረዘንቴሽን ማቅረብ ከጀመራችሁበት second አንስቶ ለ አንዴ እንኳን ወደ መምህሩ እንዳታዩ!
አንዳንድ ደ